የኦስትሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የብሪክስ ሀገራት በዩክሬን የሰላም ድርድር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ

የኦስትሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የብሪክስ ሀገራት በዩክሬን የሰላም ድርድር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ አሌክሳንደር ሻለንበርግ እንዳሉት በሩሲያ እና ዩክሬን ግጭት ዙርያ ውጤታማ የሰላም ድርድር ለማድረግ የብሪክስ ሀገራት ተሳትፎ አስፈላጊ ነው። "አንድ ግልፅ የሆነው ነገር በጠረጴዛ ዙርያ መፍትሄ ሊመጣ እንደሚገባ ነው። ይህ ብዙ አጋራትን በተለይም እንደ ሕንድ፣ ብራዚል፣ ደቡብ አፍሪካ እና ቻይናን የመሳሰሉት ሀገራት የድርድር መፍትሄ እንዲያመጡ ያሻል" ሲሉ ከዩክሬን አቻቸው አንድሪ ሲቢሃ ጋር በነበራቸው ግኑኝነት ተናግረዋል። ቀደም ሲል የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ የዩክሬንን ግጭት በመፍታት ዙርያ በብራዚል እና ቻይና የተዘጋጀውን እቅድ ከሩሲያ መሪ ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል። የሕንድ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪክራም ሚሲሪ ኒው ዴልሂ ከቁልፍ አጋር እና የመሪዎች ስብስብ ጋር በመሆን የዩክሬን ቀውስን ለመፍታት በሚደረገው ውይይት ላይ እንደተሳተፈች በዚህ ሳምንት ተናግረዋል። በውይይቱ ማን እንደተሳተፈ ግን ግልጽ አላደረጉም። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ምዕራባውያን የዩክሬንን ግጭት ለመፍታት እውነተኛ ድርድር ለማድረግ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ገልፀው ሞስኮ በዩክሬን በኩል ዝግጁነት ካየች የሰላም ኮንፈረንስ በሚካሄድበት ቦታ እና ቀን ላይ ለመስማማት ዝግጁ ነች ሲሉ በዚህ ወር መጀመሪያ ተናግረዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik