የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢጋድ ቱሪዝም ሻምፒዮን ሆነው ለሶስት ዓመታት ተሾሙ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ይፋዊ በሆነው የማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ፅሁፍ "የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለራዕይ መሪነት በቀጠናው ቱሪዝምን ለማሳደግ፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማምጣት፣ ቅርሶችን እና አካባቢን ለመጠበቅ ለሁሉም የኢጋድ አባል ሀገራት ጥቅም ወሳኝ አስተዋጽኦ ይጫወታል" ብሏል። የዐቢይ የኢጋድ ቱሪዝም ሻምፒዮን ሆኖ መሾም ይፋ የሆነው የኢጋድ ዘላቂ የቱሪዝም ፍኖተ ካርታ 2024-2034 በአዲስ አበባ ሐሙስ እለት ይፋ በሆነበት ወቅት ነው።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia