ባለፉት 2 ቀናት በሊባኖስ ውስጥ በደረሰው የመገናኛ መሳሪያዎች ፍንዳታ የ37 ሰዎች ህይወት እንዳለፈ እና በመጀመሪያው ማዕበል 12 ሰዎች እንዲሁም በሁለተኛው ማእበል ተጨማሪ 25 ሰዎች መገደላቸውን የሊባኖስ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታውቀዋል በጉዳዩ ዙርያ ባለስልጣኑ የሰጡት ተጨማሪ መግለጫዎች፦ 🟠 በመጀመሪያው ቀን ወደ ሆስፒታል የተወሰዱት ተጎጂዎች ቁጥር 2,323 ደርሷል።🟠 608 ሰዎች እሮብ እለት ቆስለዋል።🟠 1,343 የሚሆኑት ተጎጂዎች በመካከለኛ ወይም ከባድ ሁኔታ ላይ ናቸው።🟠 በሁለተኛው የጥቃት ማዕበል የገመድ አልባ መሳሪያዎች ፍንዳታ ሃይል ጠንከር ያለ በመሆኑ የከፋ ጉዳት ተመዝግቧል።መረጃውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia