የጋና ኢኮኖሚ ከአምስት ዓመት በኋላ ፈጣን ነው የተባለውን የ6.9% እድገት በ2024 ሁለተኛ ሩብ ዓመት አስመዘገበ እንደ የሀገሪቱ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ገለጻ የጋና ኢኮኖሚ ከትውልዳዊ አስከፊ የኢኮኖሚ ቀውስ አገግሟል። በማእድን ቁፋሮ እና ማውጣት መስፋፋት ምክንያት የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ከዓመት ዓመት የ9.3% እድገት ያሳየ ሲሆን የወርቅ ዘርፍ ለሶስተኛ ተከታታይ ሩብ ዓመት በመጨመሩ በሩብ ዓመቱ ከዓመት ዓመት የ23.6% እድገት አሳይቷል። የአገልግሎት ዘርፉ በ5.8% ግብርና ደግሞ 5.4% አድጓል። ይሁን እንጂ ከዓለም ሁለተኛ የኮኮዋ አምራቿ በዘርፉ በተከታታይ በአራተኛው ሩብ ዓመት ማሽቆልቆል ያሳያች ሲሆን በበሽታ እና መጥፎ የአየር ጠባይ ምክንያት ምርቱ ከዓመት ዓመት የ26.2% ቅናሽ እንዳሳየ ኤጀንሲው አመልክቷል። የኢኮኖሚው ማገገም ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር እዳዋን በአዲስ መልክ እንድታዋቅር እንደረዳት ተገልጿል። ጋና ከሁለት የቦንድ ባለቤቶች ቡድን ጋር የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ከደረሰች በኋለ 13 ቢሊየን ዶላር የሚሆነውን የሀገሪቱን ዓለም አቀፍ ቦንድ የያዙ አባዳሪዎች ቦንዱን በአዲስ እንዲለውጡ ጋብዛለች።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia