የሩሲያ ኩርስክ ክልል ነዋሪዎች በዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ምክንያት ዳቦ እንኳን ለመግዛት እንደሚሰጉ ተናገሩ ከክልሉ የሸሹ ሁለት ሴቶች ለስፑትኒክ ይህንን ተናግረዋል፦ "ቀንም ሆነ ማታ ምንም እረፍት አልነበረም። ድሮኖች ሆን ብለው መኪናዎችንና ቤቶችን ይመታሉ። ሁሌ በሚባል ሁኔታ መብራት አናበራም ነበር ማለት ይቻላል" ብለዋል። "ሲቪሎችን ብቻ ነው የሚመቱት" ሲሉ ሴቶቹ አክለዋል። በአንድ ሱቅ ውስጥ ይሰሩ ከነበሩት ሴቶች መካከል አንዷ ሰው አልባ አውሮፕላን በሱቁ ላይ ጥቃት ሲያደርስ በፍንጣሪ ቆስለዋል። ሰው አልባ አውሮፕላኑ ዳቦ በሚያደርሱበት ወቅት መውደቁን ተናግረዋል።ታሪኩን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia