ምዕራባውያን ሀገራት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ በሩሲያ እና አፍሪካ ሽብርተኝነት እንዲስፋፋ አስተዋፅዖ ማድረጋቸውን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናገሩ "አፍሪካ ከውጪ በሚመጣ ሽብርተኝነት ነው የምትሸበረው፤ ምክንያቱም ምእራባውያን የጦር መሳሪያን መነገድ እና አዳዲስ ችግሮችን መፍጠር ያዋጣቸዋል። በሽብርተኝነት ሽፋን ሃብት መዝረፍ፣ ቀውስ መዝራት፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት መፍጠር፣ በውስጣዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ መግባት ለነሱ የሚያዋጣ እና የሚቻል ነው" ሲሉ ማሪያ ዛካሮቫ በዩሬዢያ የሴቶች መድረክ ላይ ተናግረዋል። እንደ ቃል አቀባይዋ ገለጻ በ1990ዎቹ በሰሜን ካውካሰስ ክልሎች ሩሲያ የሽብርተኝነት ችግር በገጠማት ግዜ ተመሳሳይ ድርጊት ተፈጽሟል። "ሩሲያ የገጠማት አዲስ ፈተና ፍፁም አዲስ ክስተትና በምዕራባውያን አስተሳሰብ የተፈጠረው የጭቆና፣ የሀብት ምርጫ፣ የባርነት ፖሊሲ ማስፈጸሚያው የአውሮፓ ሽብርተኝነት ነው" ሲሉ ዛካሮቫ ገልጸዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia