በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ከብሪክስ ጋር የንግድ ልውውጥ እንዲጨምር አድርጓል ሲሉ የሩሲያ ባለስልጣን አስታወቁ

በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ከብሪክስ ጋር የንግድ ልውውጥ እንዲጨምር አድርጓል ሲሉ የሩሲያ ባለስልጣን አስታወቁ በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ የብሪክስ ሀገራት በሩሲያ ንግድ ውስጥ ያለቸው ድርሻ እንዲጨምር ከማድረጉም በላይ ሩሲያ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያላትን የንግድ ልውውጥ እንዲቀንስ አድርጓል ሲሉ በሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የንግድ ስምምነት ክፍል ዳይሬክተር ኢካተሪና ማዮሮቫ የሩሲያ የዓለም የንግድ ድርጅት ባለሙያዎች ማእከል ካዘገጀው መድረክ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ ተናግረዋል። ሩሲያ በምዕራቡ ዓለም የሚደርሱባትን የማእቀብ ጫናዎችን መቋቋም እንደምትችል በተደጋጋሚ ከበርካታ ዓመታት በፊት ተናግራለች። የምዕራቡ ዓለም ፀረ-ሩሲያ ማዕቀቦች ውጤታማ እንዳልሆኑ የሚገልጹ አስተያየቶች ሲሰጡም ይሰማል። የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያን የመቆጣጠር እና የማዳከም ፖሊሲ የምዕራቡ ዓለም የረዥም ጊዜ ስትራቴጂ እንደሆነ ገልጸው ማዕቀቡ በመላው ዓለም ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik