ደቡብ ሱዳን ልታካሂድ የነበረውን ብሄራዊ ምርጫን ወደ 2026 አራዘመች " በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ሊቀመንበርነት የሚመራው የሀገሪቱን የሽግግር መንግስት ሥልጣን በ2 አመት መራዘሙን እንዲሁም በታህሳስ 2024 ሊከናወን የነበረው ምርጫ ወደ ታህሳስ፣ 2026 እንዲራዘም ተደርጓል" ሲል የኪር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።መራዘሙ ስኬታማ ምርጫ ለማከናወን አስፈላጊ የሆኑ ወሳኝ ተግባራትን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ጊዜ እንደሚሰጥና በሀገሪቱ የሰላም ሂደት ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ ፈተናዎች ለመሻገር ይረዳል። "ከምርጫው በፊት አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልጋል" ሲል የኪር ጽህፈት ቤት አክሎ ገልጿል።ምንም እንኳን እ.ኤ.አ በ 2018 የተደረገው ስምምነት ለአምስት ዓመታት የዘለቀውን ግጭት ካስቆመ በኋላ በመደበኛነት ሰላም የሰፈነ ቢሆንም ፣ በተቀናቃኞቹ ማህበረሰቦች መካከል የግጭት አጋጣሚዎች መከሰታቸው ቀጥሏል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia