የኔቶ ሀገራት ዩክሬን ሩሲያን እንድታጠቃ ለመፍቀድ ሳይሆን ህብረቱ በግጭቱ ውስጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲኖረው ለመወሰን እየተወያዩ ናቸው ሲሉ ፑቲን ተናገሩ ዩናይትድ ኪንግደም ኪዬቭ የስቶርም ሻዶ ሚሳኤሎችን ሩሲያ ውስጥ በሚገኙ ኢላማዎች ላይ እንድትጠቀም ለመፍቀድ መወሰኗ ቀደም ሲል ተዘግቧል። ዩክሬን ያለ ኔቶ ሀገራት ድጋፍ በዘመናዊ ከፍተኛ አነጣጥሮ ተኳሽና የረጅም እርቀት የጦር መሳሪያዎች ጥቃት ማድረስ እንደማትችል የሩሲያው ፕሬዝዳንት ተናግረዋል። የኔቶ ሀገራት፣ አሜሪካ እና አውሮፓ በዩክሬን ግጭት ውስጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረጋቸው የጦርነቱን ባህሪ በእጅጉ እንደሚቀይር እና ከሩሲያ ጋር እየተዋጉ ነው ማለት እንደሆነ ፑቲን ጨምረው ገልጸዋል። "የሚፈጠሩብንን ስጋቶች መሰረት በማድረግ ተገቢውን እርምጃ እንወስዳለን" ሲሉም አሳስበዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia