በናይጄሪያ ቦርኖ ክልል መዲና ማይዱጉሪ የተደረመሰው የአላዉ ግድብ የጎርፍ አደጋ እንዳስከተለ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘገበ

በናይጄሪያ ቦርኖ ክልል መዲና ማይዱጉሪ የተደረመሰው የአላዉ ግድብ የጎርፍ አደጋ እንዳስከተለ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘገበ "ከዋና ከተማው 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የአላዉ ግድብ ሞልቶ በመደርመሱ በሺዎች የሚቆጠሩ የቦርኖ ክልል ዋና ከተማ ማይዱጉሪ እና አንዳንድ የጄሬ አካባቢያዊ አስተዳደር ነዋሪዎች መውጪያ አጥተዋል እንዲሁም ተፈናቅለዋል" ሲል መገናኛ ብዙሃኑ ዘግቧል። እንደ መገናኛ ብዙሃኑ ዘገባ ከሳምንት በፊት ተድርጎ በነበረ ፍተሻ የደህንነት ስጋት እንደሌለ ቢገለጽም የአላዉ ግድብ ለመደርመስ ችሏል። የክልሉ ባለስልጠናት ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ነዋሪዎች በጎርፍ ከተጥለቀለቁ አካባቢዎች እንዲርቁ የቦርኖ ክልል ፖሊስ አሳስቧል። በከባድ ዝናብ ምክንያት የደረሰው የጎርፍ አደጋ በናይጄሪያ 28 ክልሎች በትንሹ የ195 ሰዎችን ህይወት እንደቀጠፈ እና ከ207,000 በላይ ሰዎች እንደተፈናቀሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik