ቻይና ለዩክሬን ቀውስ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማግኘት የሚደረገውን ሂደት ለማመቻቸት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች "ቻይና በዩክሬን ቀውስ ዙርያ አቋሟ ወጥ እና በጣም ግልፅ ነው። ቻይና የሰላም ንግግሮችን ለማበረታታት ቁርጠኛ ነች፤ ሁሉንም የሰላም ጥረቶችም ትደግፋለች። ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ተባብሮ በመስራት ለቀውሱ ፖለቲካዊ እልባት የሚያስገኙ ሁኔታዎችን ለማጎልበት እና ለሰላም አዎንታዊ ሚናዋን ለመጫዎት ዝግጁ ናት" ሲሉ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ ተናግረዋል። የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው ሳምንት በቭላዲቮስቶክ በተካሄደው ምስራቃዊ የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር የቻይና፣ ብራዚል እና ህንድ መሪዎች የዩክሬንን ግጭት ለመፍታት ቁርጠኞች እነደሆኑ ገልጸዋል። አራቱ ሀገራት የብሪክስ ቡድን አባላት ሲሆኑ የሀገራቱ የጸጥታ ሃላፊዎች በዚህ ሳምንት በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ ይገናኛሉ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia