የቻይና አፍሪካ የንግድ ልውውጥ ከጥር እስከ ነሐሴ ወር ባለው ግዜ ውስጥ በ2.

የቻይና አፍሪካ የንግድ ልውውጥ ከጥር እስከ ነሐሴ ወር ባለው ግዜ ውስጥ በ2.7% አደገ እንደ የቻይና ጠቅላይ የጉምሩክ አስተዳደር መረጃ የቻይና አፍሪካ የንግድ ልውውጥ ከጥር እስከ ነሐሴ ወር 192.44 ቢልየን ዶላር የደረሰ ሲሆን ይህም ከዓመት ዓመት የ2.7% ጭማሬ አሳይቷል። ኤጀንሲው ያወጣው መረጃ ከቻይና ወደ አፍሪካ የሚላከው ምርት በ2.1% ቀንሶ 112.97 ቢልየን ዶላር እንደደረሰ አሳይቷል። ሆኖም ከአህጉሪቱ ወደ ቻይና የሚገቡ ምርቶች በ10.4% እድገት አሳይተው 79.47 ቢልየን ዶላር ተመዝግቧል። የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በ9ኛው የቻይና አፍሪካ ትብብር ፎረም የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ቤጂንግ ከአፍሪካ ጋር በኢንዱስትሪ፣ ግብርና፣ መሰረተ ልማት ግንባታ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብሯን ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት አስታውቀዋል። እንደ የቻይናው መሪ ገለጻ "የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ትብብር የሁሉንም ሀገራት የረጅም ጊዜ እና መሰረታዊ ፍላጎቶች ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል መንገድ ነው።" ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik