ምዕራባውያን የዩክሬን ግጭትን ለመፍታት ሐቀኛ ድርድር ለማድረግ ፈቃደኛ አይደሉም ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩሰርጌይ ላቭሮቭ በሳውዲ አረቢያ ያነሷቸው ሌሎች ነጥቦች፡-🟠 የዩክሬን ግጭት ለመፍታት ምዕራባውያን ያቀረቡት ውጥን የግጭቱ ዋና አካል የሆነውን የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች ጥበቃ ማድረግ አልቻለም።🟠 የኦላፍ ሾልዝ "የሰላም እቅድ" እና ሌሎች የምዕራባውያን ሀሳቦች በዩክሬን ውስጥ ያሉ የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪዎችን እንዲሁም "ቮልዲሚር ዘሌንስኪ የራሴ በሚለው መሬት ያሉ ችግሮችን ቸል ያሉ ናቸው 🟠 የዩክሬን ቀውስ በመሠረቱ ለመፍታት የቻይናው መሪ ዢ ጂፒንግ ያቀረቡትን ጥሪ ሩሲያ በደስታ ተቀብላለች።🟠 ከዩክሬን ግጭት ጋር ተያይዞ እርቅ ለማምጣትና የግዛት ልውውጥ ለማድረግ መወያየት ከባድ ነው🟠 ዩክሬን ሰብአዊ መብቶችን ለማስጠበቅ ፈቃደኝነት ካሳየች ሞስኮ የሰላም ኮንፈረንስ ለማካሄድ ቦታ እና ቀን መወሰን ቀላሉ ይሆናል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia