በአልጄሪያ የተካሄደው አስቸኳይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድምጽ ቆጠራ ተጀምሯልበሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ከ24 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል። እ.አ.አ መስከረም 2፣ በባህር ማዶ የሚኖሩ ከ800,000 በላይ አልጄሪያውያን ድምጽ መስጠት ጀምረዋል። ገለልተኛው የብሄራዊ ምርጫ ባለስልጣን እሁድ እለት 48.03% መራጮች መሳተፋቸውን ያወጀ ሲሆን በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቦዩ በምርጫው ያሸንፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።የምርጫ ባለስልጣኑ ሃላፊ መሀመድ ቻርፊ በመንግስት ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በባህር ማዶ የተሳተፉት መራጮች 19.57% ሲሆኑ፣ በዓለም ሀገራት መካከል ባለው የሰዓት ልዩነት ምክንያት ምርጫው አሁንም እንደቀጠለ ነው።እንደ ቻርፊ ገለጻ የተጠቀሰው ቁጥር ቅድመ ቆጠራ መሆኑን እና የመጨረሻዎቹ አሃዞች ኋላ ላይ እንደሚወጡ ተናግረዋል። ይህ የተሳትፎ መጠን በ2019 ከተደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከተመዘገበው የ39.88% የህዝብ ተሳትፎ ጋር ሲነፃፃር ቁጥሩ ይበልጣል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia