በኒጀር በደረሰ ጎርፍ ሳቢያ በትንሹ 273 ሰዎች ሲሞቱ 700,000 ያህሉ ደግሞ መፈናቀላቸው ተገልጿልአጋዴዝ በኒጀር የሰሃራ በረሃ ክፍል ውስጥ የምትገኝ በአፍሪካ ሞቃታማ እና ደረቃማ ቦታዎች አንዷ በመባል የምትታወቀው ከተማ ስትሆን አሁን በጎርፍ ተጥለቅልቃለች ሲል የማሊጄት ፖርታል ዘግቧል።በከተማዋ ያሉ ከሸክላ የተሠሩት ቤቶች ከግንቦት ወር ጀምሮ ለረጅም ጊዜ ለእርጥበት የተጋለጡ መሆናቸው እና ከባድ ዝናብ መቋቋም እንዲችሉ ተደርገው አለመሰራታቸው አብዛኛቹን ነዋሪዎች ለሞት አደጋ አጋልጧል። በጣም ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች የታሆዋ እና የማራዲ ወረዳዎች ናቸው። የጎርፍ አደጋው በሀገሪቱ ካሉት 266 ማህበረሰቦች ውስጥ 201 ያህሉን ጎድቷል፣ ከ73,000 በላይ ቤቶች አውድሟል።የኒጀር ባለስልጣናት ነዋሪዎች ለጎርፍ የተጋለጡ አካባቢዎችን ለቀው እንዲወጡ እና ለተጎዱት ዞኖች የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ እንዲሁም የነፍስ አድን ቡድኖችን እየሰማሩ ነው። በተጨማሪም ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን የምግብና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን፣ የሕክምና ድጋፍ እና ለተቸገሩት የንጽህና አገልግሎትን መሠረተ ልማቶችን በማቋቋም ላይ ናቸው። የቪዲዮ ምስሎቹ ከማህበራዊ ሚዲያ የተወሰዱ ናቸውስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia