ሞዛምቢክ የአፍሪካ ትልቁን የማንግሩቭ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ጀመረች

ሞዛምቢክ የአፍሪካ ትልቁን የማንግሩቭ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ጀመረች ሞዛምቢክ በሚቀጥሉት 60 አመታት 200 ሚሊዮን ማንግሩቭ ለመትከል ተዘጋጅታለች። ከህዳር ወር ጀምሮ በባህረ ሰላጤው ብሉ ፎረስት የሚተገበረው የሞዝብሉ ፕሮጀክት 155,000 ሄክታር (የሲንጋፖርን ሁለት እጥፍ የሚሸፍን) ሲሆን የሀገሪቱን የባህር ጠረፍ ወደነበረበት ለመመለስ ያለመ ፕሮጀክት ነው። በዚህም ለ5,000 ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥር መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። እነዚህ የማንግሩቭ ተክሎች የባህር ዳርቻዎችን ከማረጋጋት ባለፈ 20.4 ሚሊዮን ቶን ካርቦን እንደሚያስወግዱ እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ተነግሯል።የማንግሩቭ ተክል ካርቦን ዳይኦክሳይድን ለመቆጣጠር በጣም ውጤታማ ከሆኑ እፅዋት መካከል አንዱ ሲሆን፤ ያሉት ውስብስብ ሥሮቻቸው የባህር ዳርቻዎችን ያረጋጋሉ ፣ የአፈር መሸርሸርን ይቀንሳሉ እንዲሁም ለአሳ እና ለሌሎች የዱር አራዊት መጠለያ ይሆናሉ።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik