ቻይና እና ናይጄሪያ በኢንቨስትመንት እና ትብብር ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ ቻይና የናይጄሪያን የሃይል እና የማዕድን ሃብትን ለማልማት ትኩረት በማድረግ ቀዳሚ ኩባንያዎቿ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ለማበረታታት ቃል ገብታለች። ስምምነቱ የተደረሰው ከ9ኛው የቻይና-አፍሪካ ትብብር መድረክ በፊት በፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ እና ቦላ ቲኑቡ መካከል በተደረገ ውይይት ነው። ሁለቱ መሪዎች ግንኙነታቸውን እና ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ያላቸውን ከፍተኛ ፍላጎት በውይይቱ ላይ ገልጸዋል። "ቻይና እና ናይጄሪያ እንደ ቀዳሚ ታዳጊ ሀገራት ስትራቴጂክ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር በአዲሱ ዘመን ለቻይና እና አፍሪካ ግንኙነት ትኩስ መነቃቃትን መፍጠር እና በደቡባዊ ዓለም ሀገራት ውስጥ የጋራ እድገትን መምራት ይችላሉ" ሲሉ ሺ ተናግረዋል። ከሁለቱ መሪዎች ውይይት በኋላ የወጣው የጋራ መግለጫ በርካታ የትብብር መስኮችን ዘርዝሯል። ▪ ኢንቨስትመንት፦ ቻይና “ግዙፍ” ኩባንያዎቿ ናይጄሪያ ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ታበረታታለች። ▪ የፋይናንስ ትብብር፦ ሁለቱ ሀገራት በመገበያያቸው የንግድ ልውውጥ ማካሄድን ያበረታታሉ። ▪ ፀጥታና መረጋጋት፦ ቻይና የናይጄሪያን ወታደራዊ አቅም በማጎልበት የቀጠናውን ሰላምና መረጋጋት ለማስጠበቅ በጋራ ትሰራለች። ▪ ሽብርተኝነትን መከላከል፦ ሁለቱ ሀገራት ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና ለአሸባሪዎች የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍን ለመከላከል በመረጃ ልውውጥ ላይ ይተባበራሉ። ▪ መሠረተ ልማት እና ቴክኖሎጂ፦ ቻይና በቤልት እና ሮድ ኢኒሼቲቭ፣ በሰው ሃይል ልማት እና በኒውክሌር ኢነርጂ ፕሮጀክቶች የናይጄሪያን እድገት መደገፏን ትቀጥላለች። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia