የነሐሴ 29 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦

የነሐሴ 29 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የሩሲያ የጥቁር ባህር ፍሊት የሄሊኮፕተር ወታደሮች ወደ ክራይሚያ የሚጓዙ አራት የዩክሬን ሰው አልባ ጀልባዎችን ​​እንዳወደሙ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ገለጸ። 🟠 ፑቲን በሩሲያ የሩቅ ምሥራቅ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ተስፋ ሰጪ ፕሮጀክት ነው አሉ። 🟠 የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም በምስራቃዊ የኢኮኖሚ መድረክ ከፑቲን ጋር ከተገናኙ በኋላ በጥቅምት ወር ካዛን በሚካሄደው የብሪክስ ጉባኤ ላይ እንዲገኙ የቀረበላቸውን ግብዣ መቀበላቸውን አስታወቁ። 🟠 ማክሮን የፊታችን ረቡዕ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሾም ነው ተባለ። ለቦታው ግንባር ቀደም ተወዳዳሪ የሆኑት የኦ ደ ፍራንስ የክልል ምክር ቤት ሊቀመንበር እና የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የሆኑት ዛቪዬር በርትራንድ ናቸው። 🟠 የዛፖሮዝስካያ የኑክሌር ሃይል ማመንጫ ጣቢያን የጎበኙት የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ ጦርነቱ እስከጠለ ድረስ በጣቢያው የአደጋ ስጋት እንደሚኖር ተናገሩ። 🟠 የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ለዩክሬን ተጨማሪ 17 አይሪስ-ቲ ፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል ስርዓቶችን ለመስጠት ቃል መግባታቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። 🟠 ኔቶ ዩክሬን ላይ የሩሲያ ሚሳኤሎችን የመምታት ሃሳቡን አልተወም ሲሉ የሊቱዌኒያ ፕሬዝዳንት ናኡሴዳ ተናገሩ። 🟠 አዲሱ የሩሲያ ቆንስላ ጄኔራል ህንፃ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት በቱርክ አንታሊያ ከተማ ተካሄደ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik