የነሐሴ 29 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 በሩሲያ ቤልጎሮድ ግዛት ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በአንድ ጀምበር ተመትተው የወደቁ ሲሆን ተጨማሪ ሁለቱ ድሮኖች ደግሞ በኩርስክ ክልል እና በጥቁር ባህር ውሃ ላይ ተመተው መውደቃቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። በተጨማሪም የሀገሪቱ የጥቁር ባህር ፍሊት በሰሜናዊ ምዕራብ ጥቁር ባህር ክፍል አራት ሰው አልባ ጀልባዎችን አውድሟል። 🟠 ፑቲን በቭላዲቮስቶክ በሚገኘው የሩስያ ፓሲፊክ ፍሊት የጦር ሰፈር ተገኝተው ኮርቬት ሬዝኪ የጦር መርከብን መርምረዋል። 🟠 ፑቲን በምስራቃዊ የኢኮኖሚ ፎረም ምልአተ ጉባኤ ላይ ትምህርት ሰጪ ንግግር እና ውይይት እንደሚያካሂዱ ክሬምሊን አስታውቋል። 🟠 የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኩሌባ የስራ መልቀቂያ አስገቡ። 🟠 የዩክሬን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የመልሶ ማቋቋም ሚኒስትር ቬሬሽቹክም የስራ መልቀቂያ እንዳስገቡ አስታውቀዋል። 🟠 የቀድሞ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ምዕራባውያን የአታካም ሚሳኤሎችን ለኪዬቭ እንዲያስረክቡ እና የተጣሉ እገዳዎች እንዲነሱ ጠይቀዋል። 🟠 እንግሊዛዊው ዘፋኝ ኤልተን ጆን በአይን ህመም ምክንያት በከፊል ዓይነ ስውር እንደነበር ተናግሯል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia