የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሳዑዲ አረቢያ በአፍሪካ ፈሰስ ለምታደረገው በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ኢንቨስትመንት ምስጋና አቀረቡ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሳዑዲ አረቢያ በአፍሪካ ፈሰስ ለምታደረገው በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ኢንቨስትመንት ምስጋና አቀረቡ በሳዑዲ የልማት ፈንድ 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ በሪያድ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን ፕሬዝዳንት አኪንዊሚ አዴሲና ፈንዱ ከሰሃራ በታች ባሉ 41 ሀገራት በ407 ፕሮጀክቶች ላይ በድምሩ ከ5.3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት ፈሰስ እንዳደረገ ገልጸዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች ከመስኖ እና ኢነርጂ መሠረተ ልማት እስከ የጤና አገልግሎት ተቋማት፣ ትምህርት እና ትራንስፖርት ጨምሮ ብዙ ዘርፎችን ያካተቱ እንደሆነ ተናግረዋል። አዴሲና ፈንዱ የሳዑዲ-አፍሪካ ግንኙነትን ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ያደነቁ ሲሆን ይህም ቀጣይ የትብብር ፍኖተ ካርታ በነደፈው የ2023ቱ ስኬታማ የሳዑዲ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ማሳያ ነው ብለዋል። በተጨማሪም የፈንዱን ልዩ የልማት ፋይናንስ አቀራረብ አወድሰው “ያልተገደበ የግዛት ወሰን” እና የሀገሮችን ልዩ ፍላጎት ማሟላት ላይ ትኩረቱን ያደረገ እንደሆነ ተናግረዋል። ይህም ከደጋፊነት፣ ከቁርጠኝነት እና ከወዳጅነት አቀራረብ ጋር ተዳምሮ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖር አድርጓል ብለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik