የነሐሴ 28 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 ፑቲን በሞንጎሊያ ያደረጎት ይፋዊ ጉብኝት እንደተጠናቀቀ ክሬምሊን አስታወቀ። 🟠 የዩክሬን ፍትህ ሚኒስቴር፣ የስትራቴጂክ ኢንዱስትሪዎች ሚኒስቴር፣ የስነ-ምህዳር እና የተፈጥሮ ሀብቶች ሚኒስቴር እና የሀገር ንብረት ፈንድ ሚኒስቴር ሃላፊዎች ምክንያታቸውን ግልጽ ሳያደርጉ የስራ መልቀቂያ አስገቡ። 🟠 ዩናይትድ ስቴትስ የረጅም እርቀት ሚሳኤሎችን ለኪዬቭ ለማስተላለፍ ተቃርባለች ለሚሉ የመገናኛ ብዙሃን ሪፖርቶች ምላሽ የሰጠው ፔንታጐን የዩናይትድ ስቴትስ የዩክሬን ፖሊሲ እንዳልተቀየረ ግልጽ አድርጓል። 🟠 ዩክሬን 1,500 ኪሎሜትር ድረስ መወንጨፍ እና መብረር የሚችሉ ሚሳኤሎች እና ድሮኖች ሀገር ውስጥ ማምረት እንደቻለች የሀገሪቱ የስትራቴጂካዊ ኢንዱስትሪዎች ሚኒስትር አስታውቀዋል። 🟠 በአውሮፓ ሁለተኛ ትልቅ የንግድ ወደብ መቀመጫ የሆነችው የቤልጅየም ከተማ አንትወርፕ ከንቲባ የፓትሪዮት አየር መከላከያ ስርዓትን ማስተናገድ እንደሚፈልጉ ተናገሩ። 🟠 የአንካራን ብሪክስን የመቀላቀል ጥያቄ አስመልክቶ አስተያየት የሰጠው የቱርክ ገዢ ፓርቲ ያለምንም ለውጥ ውይይቶች መቀጠላቸውን አስታውቋል። ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አልተሰጠም። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia