በናይሮቢ አየር ማረፊያ የተካሄደው የስራ ማቆም አድማ የበረራ መስተጓጎል እንደፈጠረ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል በናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት የበረራ ግዜ መስተጓጎል እና ረጅም የቼኪን ሰዓት ፈጥሮ ተሳፋሪዎች ለሶስት ሰዓት ያህል ለመጠበቅ ተገደዋል። የኬንያ አቪዬሽን ሰራተኞች አውሮፕላን ማረፊያው ለህንዱ አዳኒ ግሩፕ ሆልዲንግስ ሊከራይ ነው መባሉ ስራችንን ስጋት ውስጥ ከቷል በማለት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው ተብሏል። አውሮፕላን ማረፊያው እድሳት እንደሚያስፈልገው እና የህንዱ ኩባንያ አየር ማረፊያውን ለማደስ ቁርጠኛ እንደሆነ የገለጹት የኬንያ ፕሬዝደንት ስምምነቱን ደግፈዋል። ስምምነቱ ለ30 ዓመት በሚቆይ ውል አዲስ የመንገደኞች ተርሚናል መገንባት እና ነባር መገልገያዎችን ማደስን ያካትታል። ምስሎቹ ከማህበራዊ ትስስር ገጾች የተገኙ ናቸው ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia