ቻይና የታዳጊ ሀገራትን ጥቅም ለማስጠበቅ ከአፍሪካ ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን የቻይና ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ተናገሩ "ዓለም በዋና ዋና ፈተናዎች ውስጥ በሚገኝበት ወቅት ቻይና ታሪካዊ እድሏን በመጠቀም የቻይና-አፍሪካ ትብብርን ለማሳደግ፣ የታዳጊ ሀገራትን የጋራ ጥቅም ለማስጠበቅ እና ለደቡባዊ ዓለም ሰላምና ልማት የበኩሏን አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ ነች" ሲሉ ሺ ከዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጋር ባደረጉት ውይይት ተናግረዋል፡፡ ሺ ጂንፒንግ ቻይና ዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ እና ነፃ ልማትን ለመከተል ለምታደርገው ጥረት የማያወላዳ ድጋፏን እንደምትሰጥም ገልፀዋል፡፡ በቀጣይ የሚካሄደው የቻይና አፍሪካ ጉባኤ በቻይና እና አፍሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል እድል እንደሚፈጥር አፅንዖት ሰጥተው ቁልፍ የጋራ የዘመናዊነት ጥረት እርምጃዎችን ዘርዝረዋል። ቻይና እና አፍሪካ ግንኙነታቸውን የሚያጠናክሩበት አዲስ እቅድ ለማውጣት እንደሚተባበሩም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል። የ2024ቱ የቻይና-አፍሪካ የትብብር መድረክ ከነሐሴ 29 እስከ ጳጉሜ 1 ይካሄዳል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia