ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ ግንኙነታቸውን ወደ አጠቃላይ ስትራቴጂካዊ አጋርነት አሳደጉ

ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ ግንኙነታቸውን ወደ አጠቃላይ ስትራቴጂካዊ አጋርነት አሳደጉ የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከደቡብ አፍሪካ አቻቸው ሲሪል ራማፎሳ ጋር ባደረጉት ውይይት የደቡብ ዓለም ሀገራት ውስብስብ በሆነው ዓለም ውስጥ ነፃነታቸውን፣ አንድነታቸውን እና ትብብራቸውን ማስከበር መቻላቸው አስፈላጊ እንደሆነ በአበክሮ ተናግረዋል። ዓለም አቀፋዊ ርትእ እና ፍትህ አስፈላጊ እንደሆነ የገለጹት የቻይናው ፕሬዝዳንት ሀገራቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር ቁርጠኛ እንደሆነች አረጋግጠዋል። ከውይይቱ በኋላ ሁለቱ መሪዎች የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት መሻሻል ይፋዊ ያደረገ "ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ የትብብር አጋርነት በአዲስ ዘመን" የተሰኘ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል። ሁለቱ ወገኖች የቤይዱ የሳተላይት አሰሳ ስርዓት፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ ንግድ፣ የግብርና ገበያ ተደራሽነት እና የባህል ቅርሶችን ጨምሮ በበርካታ የትብብር መስኮች ዙርያ ተፈራርመዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik