የነሐሴ 27 ረፈድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የሩሲያ አየር መቃወሚያ በቤልጎሮድ ክልል እና በጥቁር ባህር በአንድ ጀምበር ሁለት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ እንደጣለ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠 ፕሬዝዳንት ፑቲን በሩሲያ ሪፐብሊክ ቱቫ ዋና ከተማ ኪዝል ገቡ። የሀገሪቱ መሪ በአባት ሀገር ጀግኖች ስም የተሰየመውን ቁጥር 20 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚጎበኙ ሲሆን በትምህርት ቤቱ ክፍት ትምህርት እንደሚያካሂዱ እንዲሁም የኪዝል ፕሬዝዳንታዊ መኮንኖች ትምህርት ቤትን እንደሚከፍቱ ተገልጿል። 🟠 በዋስ የተለቀቀው የቴሌግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ ዱሮቭ የሪል እስቴት ወኪል ቀጥሮ በ"ውብ የፓሪስ ሰፈሮች" የመኖሪያ ቤት እየፈለገ እንደሆነ እና እስከሚመጣው ሳምንት መጨረሻ በአዲሱ ቤት ይገባል ብሎ እንደሚጠብቅ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። 🟠 የደቡብ ኮሪያ ፖሊስ ፈረንሳይን ተከትሎ በቴሌግራም ላይ የራሱን ምርመራ እንደጀመረ እና ጉዳዩ ከዲፕሎማሲ ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን ማመቻቸት እንደሚመለከት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። 🟠 በፕሬዝዳንት አሊዬቭ የሚመራው የአዘርባጃን ገዥ ፓርቲ በሀገሪቱ ፓርላማ ከ125 መቀመጫ 68ቱን በማግኘት አብላጫውን እንደያዘ እና የተሳታፊዎች ቁጥር ከ37% በላይ እንደነበር ከ91% የምርጫ ጣቢያዎችን መረጃ መሰረት አድርጎ የሀገሪቱ ማዕከላዊ ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል። 🟠 የሩሲያ መንግሥት ድርጅት ሮስቴክ ለሩሲያ አየር ኃይል ለአየር ቦምቦች የተዋሃደ የእቅድ እና ማስተካከያ ሞጁል ይውላሉ የተባሉ የሱ-34 አውሮፕላኖችን አስረከበ። 🟠 የእንግሊዝ የባህር ኃይል በየመን የባህር ዳርቻ አቅራቢያ የንግድ መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia