ለኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ሞት ምክንያት የሆነው የሄሊኮፕተር አደጋ በመጥፎ የአየር ሁኔታ እንደተከሰተ መርማሪዎች ደመደሙ

ለኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ሞት ምክንያት የሆነው የሄሊኮፕተር አደጋ በመጥፎ የአየር ሁኔታ እንደተከሰተ መርማሪዎች ደመደሙ የመንግሥት የዜና ወኪል አይሪቢ ያሳተመው የኢራን የጦር ኃይሎች ሪፖርት በሰሜን ምዕራብ ኢራን የነበረው መጥፎ የአየር ሁኔታ እና ድንገተኛ ጭጋግ ሟቹን ፕሬዝዳንት የጫነው ሄሊኮፕተር ተራራ ላይ እንዲከሰከስ አድርጓታል ብሏል። ግንቦት ወር ላይ በደረሰው አደጋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶሌን እና ሌሎች በርካታ የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ይህም አስቸኳይ ምርጫ እንዲካሄድ አስገድዷል። የምርመራው ውጤት ለኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ ይቀርባል ተብሏል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik