ሃማስ በጋዛ ለታጋቾች ሞት እስራኤልን ተጠያቂ አደረገ

ሃማስ በጋዛ ለታጋቾች ሞት እስራኤልን ተጠያቂ አደረገ የፍልስጤም እንቅስቃሴ የፖለቲካ ቢሮ አባል አል-ሪሼቅ እሁድ እለት እንደተናገሩት "በእንቅስቃሴው ለታሰሩት ታጋቾች ሞት ሀላፊነቱን የምትወስደው የዘር ማጥፋት ጦርነቱ እንዲቀጥል አጥብቃ የምትፈልገውወራሪዋ [እስራኤል] ናት" ብለዋል። የሐማስ ባለስልጣን በእስራኤል የቦምብ ጥቃት ታጋቾች እየሞቱ እንደሆነ ተናግረዋል። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እስራኤልን በገንዘብና ጦር መሳሪያ መደገፍ እንዲያቆሙ እና በጋዛ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እንድታቆም ግፊት እንዲያደርጉ አሳስበዋል። እስራኤል ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የሮኬት ጥቃት እና ወረራ መስከረም 26 ቀን ደርሶባታል። የሃማስ ተዋጊዎች በወታደራዊ እና በሲቪል ኢላማዎች ላይ ተኩስ ከፍተው ከ250 በላይ ታጋቾችን በሃይል ወስደዋል። እስራኤል 1,200 ሰዎች ተገድለዋል ብላ ትገምታለች። እስራኤል ለሃማስ ጥቃት ምላሽ በጋዛ ባካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ ከ40,000 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik