የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ለብሄራዊ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ወደ ቻይና የሚያደርጉትን ጉዞ ሰረዙኢብራሂም ትራኦሬ በቅርቡ በባርሳሎሆ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የብሄራዊ ደህንነት ችግሮችን ለመፍታት እንዲህ አይነት ውሳኔ ማሳለፍቸው ተዘግቧል። እ.አ.አ ከመስከረም 4-6 በቤጂንግ ሊካሄድ በታቀደው የቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም ላይ አይሳተፉም።እንደ ዘገባው ከሆነ በቡርኪናፋሶ ማዕከላዊ-ሰሜን ክልል ባርሳሎጎ ከተማ ላይ እ.አ.አ በነሀሴ 24 በደረሰው ጥቃት እስከ 200 የሚደርሱ ንፁሃን ዜጎች እና የጸጥታ አባላት ተገድለዋል። ይህ ክስተት በቡርኪናፋሶ እየተካሄደ ያለው ግጭት አንዱ አካል ሲሆን ከአልቃይዳ* እና ዳኢሽ* ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂ ቡድኖች ገጠራማ አካባቢዎች ዒላማ. በማድረግ ለከፍተኛ ብጥብጥ እና መፈናቀል ምክንያት ሆነዋል።* የአሸባሪ ድርጅቶች በሩሲያ እና በሌሎች በርካታ ሀገራት እገዳ ተጥሎባቸዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia