ሩሲያ የብሪክስ አጋሮችን የከተማ ልማት ልምድ ለመቅሰም ፍላጎት እንዳላት ገለጸች የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ከነሐሴ 21-22 በሞስኮ በሚካሄደው 6ኛው ዓለም አቀፍ የከተማ አስተዳደሮች የብሪክስ ፎረም ላይ ለተሳታፊዎች በቪዲዮ መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት የተናገሩት ነው። ሚኒስትሩ "የወዳጆቻችንን ልምድ ለመተግበር ፍላጎት አለን። እንደዚህ ያሉ እርስ በርስ የሚያጎለብቱ ልውውጦች አስፈላጊነት ግልፅ ነው" ብለዋል። "በብሪክስ ከተሞች እና ክልሎች መካከል ያለው ትብብር በጥንካሬ እያደገ እና በስብሰቡ አጀንዳ ውስጥ ወሳኝ ቦታ የተሰጠው ነው" ሲሉም ተናግረዋል። እንደ ላቭሮቭ ገለጻ ዓለም አቀፋዊው ፈጣን የከተሜነት መስፋፋት አዝማሚያ "ለከተሞች ዘላቂ ልማት እና ለነዋሪዎች ምቹ የከተማ አካባቢን መፍጠር የሚያስችል የረጅም ጊዜ እና በአግባቡ የተጠና ፖሊሲ ይፈልጋል።" በዚህ ረገድ የብሪክስ ሀገሮች ዓለም አቀፍ የከተማ አስተዳደሮች ፎረም አስፈላጊ እንደሆነ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አፅንዖት ሰጥተዋል። "ሁሉም እንግዶቻችን የመዲናችንን እንግዳ ተቀባይነት እንደሚያጣጥሙ እርግጠኛ ነኝ። መድረኩ ጠቃሚ ግንኙነቶችን ለመመስረት፣ ተስፋ ሰጭ በሆኑ የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ ለመስማማት፣ በህዝቦቻችን መካከል ወዳጅነት እና መተማመን የበለጠ ለማጠናከር ተጨማሪ እድሎችን ይፈጥራል" ሲሉ ላቭሮቭ አጠቃለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia