ኢትዮጵያ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ሁለት አዳዲስ ተርባይኖች ስራ አስጀመረች

ኢትዮጵያ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ሁለት አዳዲስ ተርባይኖች ስራ አስጀመረች እንደ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጻ የታላቁ ህዳሴ ግድብ 3ኛ እና 4ኛ ተርባይኖች ተከፍተው በሰከንድ ተጨማሪ 2,800 ኪዩቢክ ሜትር ውሃ መልቀቅ ጀምረዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ፍሰትን በመቆጣጠር፣ የጎርፍ አደጋ ስጋትን በመቀነስ፣ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በተለይ በድርቅ ዘመን መጠኑ ያልዋዠቀ የውሃ አቅርቦት እንዲደርሳቸው ያደርጋል ሲሉም አፅንኦት ሰጥተዋል። የተርባይኖቹ ስራ መጀመር የግብር ምርታማነትን፣ የኃይል የማመንጨት ሥራን እና በቀጠናው የሀብት አጠቃቀምን ለማጎልበት በእጅጉ ይጠቅማል ብለዋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በኢትዮጵያ እና በታችኛው ተፋሰስ ጎረቤት ሀገራት ሱዳን እና ግብፅ መካከል በውሃ አቅርቦት እና ቁጥጥር ዙርያ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ አለመግባባትን ፈጥሮ ቆይቷል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik