ኡጋንዳ እና ሩሲያ ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል

ኡጋንዳ እና ሩሲያ ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋልብዙ ቁጥር ያለው የሩሲያ ወታደራዊ ልዑክ በአፍሪካዊቷ ሀገር ኡጋንዳ ጉብኝት አድርጓል። ልዑኩ ከኡጋንዳ ህዝብ መከላከያ ሃይል (UPDF) መሪ ጋር እ.አ.አ ነሀሴ 22 ተገናኝቷል። በሩሲያ የመከላከያ ሚኒስትር አንድሬይ ቤሉሶቭ የተላከው የልዑካን ቡድን "በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር" የሚል ኃላፊነት እንደተሰጠው የኡጋንዳ ህዝብ መከላከያ ሃይል ተናግሯል።ጉብኝቱ የኡጋንዳ ጦር አዛዥ ጄኔራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ሞስኮ ያደረጉትን ጉዞ ተከትሎ የተከናወነ ነው። የሀገሪቱ የልዩ ሃይል አዛዥ ከሩሲያ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ጋር በቅርቡ ምክክር ማድረቸውን የኡጋንዳ ህዝብ መከላከያ ሃይል አስታውቋል።በሞስኮ እና በካምፓላ መካከል ያለው ግንኙነት በ1960 ዎቹ የጀመረ ሲሆን ፤ ዩጋንዳ የሩሲያን ጄቶች፣ ሄሊኮፕተሮች፣ መድፎች እና የስለላ መሳሪያዎችን ትገዛለች።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik