የዓለም ጤና ድርጅት በሱዳን አዲስ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ 658 ሰዎች መያዛቸውን እና 28 ሰዎች ደግሞ መ ሞታቸውን አስታወቋል

የዓለም ጤና ድርጅት በሱዳን አዲስ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ 658 ሰዎች መያዛቸውን እና 28 ሰዎች ደግሞ መ ሞታቸውን አስታወቋል"አሁን እ.አ.አ ነሐሴ 12 በይፋ የታወጀውን ሁለተኛ ዙር የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታን እየተመለከትን ነው ... እ.አ.አ እስከ ትናንት ነሐሴ 22 ቀን ድረስ 658 በበሽታው የተያዙ ሲሆን 28 ሰዎችደግሞ መሞታቸውን ሪፖርት አድርገናል። ... ይህ የበሽታውን የመግደል ምጣኔን 4.3% የደረሰው ሲሆን ከፍተኛ የሚባል መጠን ነው። ወረርሽኙ በእርግጥ በብዙ ምክንያቶች የተከሰተ ሲሆን ይህም የተበላሸውን የጤና ስርዓት እና ምላሽ የመስጠት አቅም መዳከም ከብዙ በጥቂቱ የሚነሱ መንስኤዎች መሆናቸውን"በሱዳን የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ሺብል ሳህባኒ በጄኔቫ በሰጡት አጭር መግለጫ ወቅት ተናግረዋል።በሽታው በሱዳን በአምስት ክልሎች መስፋፋቱን የገለፁት የዓለም ጤና ድርጅት ባለስልጣን በሽታው እ.አ.አ በመስከረም 2023 ከታወጀውና በግንቦት 2024 ካበቃው የመጀመሪያው የኮሌራ ወረርሽኝ ጋር ግንኙነት እንደሌለው ተናግረዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik