የሩሲያ የባህር ኃይል በሱዳን የባህር ኃይል ሰፈር በቅርቡ ሊያቋቋም እንደሚችል የሩሲያ ኤምባሲ አስታወቀበሩሲያ እና በሱዳን መካከል ያለው ስምምነት አሁንም እንደተጠበቀ መሆኑን በሱዳን የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ለሩሲያ የዜና ማሰራጫ "ኢዝቬሺያ" ገልጿል።"የዚህ ስምምነት ተፈፃሚነት በሁለቱም ሀገራት ባሉ የተወሰኑ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ እና በማንኛውም ጊዜ ሊወሰን የሚችል ነው" ሲል ኤምባሲው ገልጿል።በተጨማሪም ሱዳን ከሩሲያ ጋር የጀመረችውን የኢንተርስቴት ስምምነት ለመሰረዝ እንዳሰበች የሚነገረውን የምዕራባውያን ወሬ በተደጋጋሚ ውድቅ ማድረጓን ኤምባሲው አመልክቷል።ሱዳን ለሩሲያ የባህር ኃይል የሎጂስቲክስ ድጋፍ ሰጪ ማዕከል እንዲሆን መጀመሪያ ላይ ስምምነት ላይ የተደረሰው እ.አ.አ በታህሳስ 2020 መጀመሪያ ላይ ነበር። ይህ የሎጂስቲክስ ድጋፍ ሰጪ ማዕከል የተቀረው የሩሲያ መርከቦችን ለመጠገን እና ለመርከበኞች ማረፊያ የታሰበ ነው። በስምምነቱ መሰረት የባህር ኃይሉ ሰፈር ቢበዛ 300 ሰራተኞችን የሚያስተናግድ ሲሆን በአንድ ጊዜ እስከ አራት የሩሲያ መርከቦችን ያስተናግዳል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia