ኬንያ በ2034 የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት አቅዳለች የካቢኔ ፀሀፊ ሙሳሊያ ሙዳቫዲ በ2034 የኬንያ የመጀመሪያውን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት ማቀዷን እና እ.አ.አ በ 2030 መጀመሪያ ላይ ደግሞ የኒውክለር ምርምር አክተሩ ሥራ እንደሚጀምር አስታውቀዋል።ይህ 1,000 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጫ ፋብሪካ 500 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ (3.9 ቢሊዮን ዶላር) የሚገመተው መሆኑን መገናኛ ብዙሃን ግምታቸውን ያስቀመጡ ሲሆን፤ የኃይል አቅርቦትን ለማሳደግ፣ የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ እና የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያለመ ነው። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ሀገሪቱ በ2030 100% ታዳሽ ሃይልን የማሳካት አቅም እንዳላት ቀደም ብለው ተናግረዋል። የጥር ወር የኬንያ ብሄራዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ እንደሚያመለክተው በ2023 የመጀመሪያዎቹ 11 ወራት 706.9 ሚሊዮን ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ከኢትዮጵያ እና ከኡጋንዳ ያገኘት ሲሆን ይህም ከ2022 ጋር ሲነፃፀር ወደ 2.5 ጊዜ የሚጠጋ ጭማሪ አሳይቷል። አብዛኛው ሃይል የተገኘው ከኢትዮጵያ ነው። በመጋቢት ወር የኬንያ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኩባንያ በ2026 ከኢትዮጵያ የሚመጣውን የኤሌክትሪክ ኃይል ከ200 ሜጋ ዋት ወደ 400 ሜጋ ዋት ለማሳደግ ማቀዱን አስታውቋል። በዚህም የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በ2026 በእጥፍ ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia