በኒጀር በደረሰው ጎርፍ በትንሹ 131 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል

በኒጀር በደረሰው ጎርፍ በትንሹ 131 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯልከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በኒጀር በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ሌሎች 133 ሰዎች መጎዳታቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።የጎርፍ አደጋው ወደ 32,000 የሚጠጉ አባወራዎችን መጎዳቱን የሀገሪቱ የሲቪል መከላከያ እና የአደጋ መከላከል መምሪያ አስታውቋል።በህንፃ መደርመስ ሳቢያ 80 ያህል ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 51 ሰዎች ደግሞ ሰጥመው ሞተዋል። ወደ 27,000 የሚጠጉ ቤቶች እና የመኖሪያ ሕንፃዎችም ፈርሰዋል። በጎርፍ አደጋው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሃንጋሮች እና ሱቆች ተጎድተዋል። በተጨማሪም የኒጀር የትራንስፖርት ሚኒስትር ሳሊሱ መሃማን ሳሊሱ ማክሰኞ እለት የተጠገኑትን የሶሪ እና ንዶውንጋ መንገዶችን ጎብኝተዋል ሲል የሀገሪቱ የዜና ወኪል ኤኤንፒ ዘግቧል።ብሄራዊ መንገዶች 1 እና 31 በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ተበላሽተዋል። በተቻለ ፍጥነት መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ክፍት እንዲሆኑ አስፈላጊውን እርምጃዎች ሁሉ ይወሰዳሉ ሲሉ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። ሰኞ እለት በኒያሚ የሚገኘው የውሃ መጠን 620 ሴ.ሜ ደርሷል፤ በዚህም የቀይ ማንቂያ ደረጃ በወንዝ ዳር ለሚገኙ ነዋሪዎች የጎርፍ አደጋ ስጋት እንዳለው በኒያሚ የሚገኘው የአግሪሜት ማእከል ባለሙያ ተናግረዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik