በዩክሬን የሚገኘው የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ ኤም ኤፍ) ኃላፊ ኪየቭ ግብር ለመጨመር ያቀደችውን እቅድ እንደሚደግፉ ተዘግቧል

በዩክሬን የሚገኘው የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ ኤም ኤፍ) ኃላፊ ኪየቭ ግብር ለመጨመር ያቀደችውን እቅድ እንደሚደግፉ ተዘግቧልበዩክሬን የሚገኘው የአይኤምኤፍ ተልእኮ ኃላፊ ጋቪን ግሬይ የዩክሬን መንግስት ግብር ለመጨመር ያቀደውን እቅድ መደገፉን የዩክሬን መገናኛ ብዙሃን ማክሰኞ እለት ዘግበዋል። እ.ኤ.አ ሐምሌ 18 የዩክሬን የፓርላማ አባል ያሮስላቭ ዜሌዝኒያክ የዩክሬን መንግሥት ግብርን ለመጨመር የሚያስችል ረቂቅ አዘጋጅቷል ብለዋል፤ በተለይም የወታደራዊ ታክስ መጠንን ከፍ ለማድረግ ሀሳብ አቅርቧል። በእለቱ የዩክሬን መንግስት የፓርላማ ተወካይ ታራስ ሜልኒቹክ እንደተናገሩት መንግስት የመከላከያ ወጪን በ495.3 ቢሊዮን ሂሪቪንያ (12 ቢሊዮን ዶላር) ለማሳደግ የሚያስችል ህግ ማፅደቁን ተናግረዋል። እ.ኤ.አ ነሐሴ 1 የዩክሬን ፋይናንስ ሚኒስትር ሰርጊ ማርቼንኮ ለአገሪቱ የጦር ኃይሎች የገንዘብ ድጋፍ የሚሆን ምንጮች ስለተሟጠጡ ከህዝቡ የሚሰበሰበውን ግብር ማሳደግ አስፈላጊ ነው ማለታቸው ይታወሳል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik