ዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ የመጀመርያውን የኤምፖክስ ​​ክትባት በሚቀጥለው ሳምንት እንደምትረከብ ተገለጸ

ዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ የመጀመርያውን የኤምፖክስ ​​ክትባት በሚቀጥለው ሳምንት እንደምትረከብ ተገለጸ ጃፓን እና ዩናይትድ ስቴትስ ክትባቶችን ለኮንጎ ለማቅረብ ቃል እንደገቡ የጤና ሚኒስትሩ ሳሙኤል ሮጀር ካምባ ሙላምባ ሰኞ እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። "ከዩኤስአይዲ እና የአሜሪካ መንግሥት ጋር ውይይታችንን ጨርሰናል...በሚቀጥለው ሳምንት ክትባቶቹ ይደርሳሉ ብለን ተስፋ እንደርጋለን" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የእነዚህ ክትባቶች አቅርቦት በ2022ቱ ዓለም አቀፍ የኤምፖክስ ወረርሽኝ በአውሮፓ እና አሜሪካ ጥቅም ላይ የዋሉት ሁለት ክትባቶች አፍሪካን በማግለላቸው የተፈጠረውን ልዩነትን ለመቅረፍ ያለመ ነው። የዓለም አቀፍ የክትባት ህብረት ጋቪ፤ በአፍሪካ እየጨመረ በመጣው የኤምፖክስ ወረርሽኝ ለተጠቁ ሀገራት ክትባቶችን ለመግዛት 500 ሚልዮን ዶላር እንደተመደበ ባለፈው ሳምንት ለምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን አስታውቋል። የዲአር ኮንጎ የጤና ሚኒስትር "ጋቪ ክትባቶቹን ለማቅረብ ጥያቄ አቀረበ፤ እኛም ተስማማን" ሲሉ ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik