የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የመጀመሪያውን ራዳር ኢሜጂንግ ሳተላይት ወደ ህዋ አመጠቀች የሲንቴቲክ አፐርቸር ራዳር (ሳር) የተሳካ የህዋ ጉዞ ከካሊፎርኒያ ቫንደንበርግ የጠፈር ጣቢያ ተካሂዷል። በስፔስኤክስ ትራንስፖርተር 11 ሮኬት ተሳፍሮ የመጠቀው ሳተላይት በኤአይ የታገዘ የጂኦስፓሻል መፍትሄ አቅራቢ በሆነው ባያናት እና በጠፈር ኮሚኒኬሽን ኩባንያው ያሳት የጋራ ትብብር ውጤት ነው። የህዋ ተልእኮው የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ወደ ምድር ምልከታ ሳተላይት ቴክኖሎጂ መግባቷን ያመለከተ ሲሆን ይህም የጠፈር አቅሟን ከ2020 ማርስ ተልእኮ የበለጠ የሚያሰፋ ነው ተብሏል። የሳር ሳተላይት የላቀ ኢሜጂንግ እና የመረጃ ትንተና አቅሞችን በመስጠት የአካባቢ ቁጥጥር፣ የአደጋ አስተዳደር እና የሀብት አያያዝን ጨምሮ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን አቅም በተለያዩ ዘርፎች የበለጠ ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia