የነሐሴ 13 ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የሩሲያ አየር መቃወሚያ በቤልጎሮድ እና ኩርስክ ክልሎች ላይ አራት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በአንድ ምሽት ውስጥ እንዳወደመ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። በኦሬል ክልል ተጨማሪ የሰው አልባ አውሮፕላን መውደሙን የክልሉ አስተዳዳሪ ገልጸዋል። 🟠 ፖላንድ የሩሲያ ሚሳኤሎችን በዩክሬን የአየር ክልል ለማጨናገፍ የምትሞክር ከሆነ ሞስኮ ተጨባጭ እና በቂ ምላሽ እንደምትሰጥ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠 የዩክሬን የመረጃ እና የስነ-ልቦና ኦፕሬሽን ሰራተኞች በሱሚ ክልል ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል የውጭ ጋዜጠኞችን በማሰማራት የሩሲያ ጦር በኩርስክ ክልል የራሱን ህዝብ እየደበደበ እንደሆነ ለመዘገብ ከሩሲያ እስረኞች ጋር የተቀነባበረ ቀረጻ እንዳካሄዱ ለጉዳዩ እውቀት ያለው ምንጭ ተናግሯል። 🟠 ሩሲያ የኖርድ ስትሪም የቦምብ ፍንዳታ ምርመራን በተመለከተ ለጀርመን በይፋ ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን ጀርመን ዓለም አቀፍ የፀረ ሽብርተኝነት ግዴታዋን መወጣት በምትችለበት ሁኔታ ላይ ውይይት የማድረግ ግብ እንዳለው የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠 ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ሩሲያ በዛፖሮዢያ የኑክሌር ማብለያ ጣቢያ በተነሳው እሳት ተሳትፎ እንደሌላት አረጋግጧል። 🟠 የሩሲያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት የክሉኒ ፋውንዴሽን ለፍትህ የተሰኘው አሜሪካ መቀመጫውን ያደረገው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እንቅስቃሴ አላስፈላጊ እንደሆነ ወሰነ። 🟠 ኤለን መስክ ለሩሲያ ቼቼን ሪፐብሊክ መሪ ራምዛን ካዲሮቭ ቴስላ ሳይበር ትራክን አልሰጠሁም ብሏል። 🟠 ከዴሞክራቲክ ፓርቲ ብሔራዊ ኮንቬንሽን በፊት በቺካጎ በተካሄደው የፍልስጤም የድጋፍ ሰልፍ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia