ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት እውቅና ሳትሰጥ ለመደራደር ፍቃደኛ እንዳልሆኑ የሶማሊያ መሪ ገለጹ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ "ለሙሉ ሉዓላዊነታችን እውቅና ሳትሰጥ ከኢትዮጵያ ጋር በማንኛውም ጉዳይ አንደራደርም" ማለታቸውን ጠቅሶ የዘገበው ሶና የዜና ወኪል ነው። እንደ ዜና ወኪሉ ዘገባ ከሆነ፤ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት እውቅና አለመስጠቷ በአንካራ "በቅርቡ የተካሄደው ድርድር እንዳይሳካ" ምክንያት እንደነበር የሶማሊያው ፕሬዝዳንት አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህ መግለጫ በቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬቼፕ ጣይብ ኤርዶአን አነሳሽነት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ድርድር እየተካሄደ ባለበት ወቅት የመጣ ነው። ሁለተኛው ዙር ድርድር ሰኞ እና ማክሰኞ በአንካራ ተካሂዷል። የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን እንዳስታወቁት፤ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ለማስታረቅ የተጀመረው ድርድር ሶስተኛ ዙር መስከረም 7 ቀን በአንካራ ይካሄዳል። ቀደም ሲል ኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ሰሜናዊ ምዕራብ ክፍል የምትገኘው ሶማሌላንድ፤ ለአዲስ አበባ የቀይ ባህር መዳረሻ የሚያስገኝ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ይህን ተከትሎ የሶማሊያ ባለስልጣናት በአዲስ አበባ የሚገኙትን አምባሳደር የጠሩ ሲሆን ሼክ ሞሀሙድ በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል የተደረገውን ስምምነት የሚሽር ህግ ፈርመዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia