ሱዳን ከቻድ ጋር የሚያገናኛትን ድንበር ለሰብዓዊ እርዳታ ክፍት አደረገች

ሱዳን ከቻድ ጋር የሚያገናኛትን ድንበር ለሰብዓዊ እርዳታ ክፍት አደረገች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥያቄ መሰረት የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ከቻድ ጋር የሚያገናኘውን የአድሬ ድንበር መተላለፊያን ለሶስት ወር ለመክፈት እና በምእራብ የሀገሪቱ ክፍል በግጭት ለተጎዱ ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ እንዲገባ ተስማምቷል። መተላለፊያው እ.አ.አ ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ ከሀገሪቱ ጦር ጋር ግጭት ውስጥ ለሚገኘው አማፂው የፈጥኖ ደራሽ ሃይል የጦር መሳሪያ ማስገብያ ነው በማለት ስጋታቸውን የገለጹት የሱዳን ባለስልጣናት በመጀመሪያ ድንበሩን ላለመክፈት አቅማምተው ነበር። እንደ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት መግለጫ የሀገሪቱ የሰብዓዊ እርዳታ ኮሚሽን "በተለመደው እና ስምምነት በተደረሰበት ቁጥጥር" መሰረት አድሬ መታላለፊያን በመክፈት እርዳታው ለታለመላቸው ሰዎች መድረሱን እንዲያረጋግጥ አቅጣጫ ተሰጥቶታል። እርምጃው የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች በቅርብ ግዜያት በታይን ማቋረጫ በቻድ በኩል የሚገባውን እርዳታ ለመጨመር ያደረጉትን ጥረት ተከትሎ የመጣ ሲሆን መተላለፊያው በከባድ ዝናብ ምክንያት የሎጂስቲክስ ችግር እንደገጠመው ተገልጿል። የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ከጎረቤት ቻድ ጋር በሚያዋስነው ድንበር በኩል ለፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ወታደራዊ መሳሪያ ታቀርባለች ሲል የሱዳን መንግሥት ከዚህ ቀደም ክስ አቅርቧል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik