የእስራኤል ሰው አልባ አውሮፕላኖች በደቡባዊ ሊባኖስ ባደረሱት ጥቃት 3 ሰዎች መሞታቸውን አንድ ምንጭ ገለጸረቡዕ ዕለት አንድ የእስራኤል ሰው አልባ አውሮፕላን በከተማው መሃል አንድ መኪና ላይ ጥቃት ማድረሱን የዜና ምንጩ ዘግቧል። "በእስራኤ ሰው አልባ አውሮፕላን ማርጃዩን አካባቢ ባደረሰው ጥቃት በመኪናው ውስጥ የነበሩ 3 ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች ደግሞ መቁስላቸውን ምንጩ ለስፑትኒክ ተናግሯል።ቅድመ መረጃው እንደሚያመለክተው የተገደሉት ሦስቱ ሰዎች በሊባኖስ የሚገኘው የፍልስጤም ንቅናቄ የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ አል-ጀማአህ አል ኢስላሚያህ አባላት ናቸው።በአጠቃላይ፣ እሮብ እለት እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ ላይ ባደረሰቸው ጥቃት፣ የሊባኖስ የህክምና ድንገተኛ አደጋ ማዕከል እንደገለጸው፣ አራት ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 27 ሰዎት ደግሞ መቁሰላቸውን ሲገልፁ፤ ከእነዚህ ውስጥ ዘጠኙ በጠና ሁኔታ ላይ የሚገኙ ናቸው።ረቡዕ እለት ቀደም ብሎ የእስራኤል ሰው አልባ አውሮፕላን በአባሲዬህ መንደር ጥቃት አድርሷል። እንደ ድንገተኛ የህክምና ማእከል ከሆነ በጥቃቱ 10 ሰዎች መቁሰላቸውን እና ከነዚህም ውስጥ 3ቱ በጠና ሁኔታ ሆስፒታል መግባታቸው ተገልጿል። በምላሹም የሊባኖስ ሂዝቦላህ ንቅናቄ ተዋጊዎች ረቡዕ ዕለት በእስራኤል ጦር ላይ አራት የውጊያ ዘመቻዎችን አድርገዋል። እንዲሁም በአባሲዬ ለደረሰው ጥቃት ምላሽ በእስራኤል ድንበር ላይ የሚገኘውን የቂርያት ሽሞና መንደር ተኩስ ከፍተዋል።ምስሎቹ ከማህበራዊ አውታረመረቦች የተገኙ ናቸውስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia