የነሀሴ 9 ረፈድ ዋና ዋና የአለም ዜናዎች🟠 የሩሲያ ጤና ጥበቃ ድርጅት በዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ለተጠቁ የአፍሪካ ሀገራት ስፔሻሊስቶችን በማሰልጠን እገዛ እና ድጋፍ ለማድረግ ሀሳብ አቅርቧል። የዓለም ጤና ድርጅት ከአንድ ቀን በፊት የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ አሳሳቢ የህዝብ ጤና ስጋት መሆኑን ማወጁ ይታወሳል።🟠 ቻድ ሞሮኮ በግዛቷ ላይ ያላትን መብት የሚደግፉ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራትን በመቀላቀል በምዕራብ ሳሃራ ቆንስላ ከፈተች።🟠 ካሜሩን እ.አ.አ በ2030 ሀገሪቱን በሙዝ እንዲሁም ፕላንቴይን ምርት ወደ ግንባር ቀደም አምራችነት ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ትኩረት እንደምትሰጥ የግብርና ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።🟠 የቡርኪናፋሶ መንግስት በሀገሪቱ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እንዲቋቋም አዋጅ አጽድቀዋል።🟠 በሩሲያ ቤልጎሮድ ክልል ሼቤኪኖ ላይ በደረሰ የድሮን ጥቃት አራት ንፁሀን ዜጎች መቁሰላቸውን ገዥው አስታውቀዋል።🟠 ዘሌንስኪ የኖርድ ስትሪም የነዳጅ ማስተላለፊያ የማበላሸት እቅድን ማፅደቁን እና ይህንን ጉዳይ ሲአይኤ ካወቀ በኋላ ግን ውሳኔውን ለመሰረዝ ሞክሯል ሲል የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።🟠 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ በተቀናቃኛቸው እና በዲሞክራቲክ እጩ ካማላ ሃሪስ የሚያሸንፉ ከሆነ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ አያገግምም ብለዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia