የዩክሬን ሩሲያ ግዛት ውስጥ መግባት “እውነተኛ አጣብቂኝ” እየፈጠረ ነው ሲሉ ባይደን ተናገሩ "ላለፉት ስድስት ወይም ስምንት ቀናት ውስጥ በየአራት ወይም አምስት ሰአታት ልዩነት ከባልደረቦቼ ጋር በመደበኛነት እናወራለን። ፑቲንን እውነተኛ አጣብቂኝ ውስጥ እየከተተው ነው። ከዩክሬናውያን ጋር ቀጥተኛ እና ተከታታይ ግንኙነት ነበረን ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዩክሬን ጥቃት ዙሪያ ማክሰኞ ዕለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።ማክሰኞ ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ቃል አቀባይ ቬዳንት ፓቴል ዩናይትድ ስቴትስ በኩርስክ ክልል ውስጥ በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ አላደረገችም ማለታቸው ይታወሳል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia