የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች አዛዥ በጄኔቫ በሚደረገው የተኩስ አቁም ድርድር ላይ የሱዳን መደበኛ ሰራዊት እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረበ

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች አዛዥ በጄኔቫ በሚደረገው የተኩስ አቁም ድርድር ላይ የሱዳን መደበኛ ሰራዊት እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረበ"የሰላምን በር በፍፁም አንዘጋውም። ስለዚህ አሜሪካ እ.አ.አ ነሀሴ 14 በጄኔቫ የተኩስ አቁም ንግግር እንዲደረግ ያቀረበችውን ግብዣ በድጋሚ ተቀብያለሁ...ሌላው ወገን ለቀረበው ጥሪ ምላሽ እንዲሰጥ በዚህ አጋጣሚ እንጠይቃለሁ። ” ሲሉ ጄኔራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ በኤክስ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።የአሜሪካ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ቶም ፔሪዬሎ በጄኔቫ ለጋዜጠኞች እንዳስታወቁት የሱዳን ታጣቂ ሃይሎች እ.ኤ.አ ነሐሴ 14 ቀን በጄኔቫ በሚካሄደው ውይይት ላይ እንደሚሳተፉ አላረጋገጡም፤ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች ግን እንደሚገኙ አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ ሁለቱም ወገኖች ሳይገኙ መደበኛ ሽምግልና ሊቀጥል እንደማይችል ልዩ መልዕክተኛው ገልፀዋል።በሱዳን ጉዳይ የሚደረገው ድርድር የልዑካን ቡድኑ በተስማሙበት አጀንዳ ዙሪያ እስከ ነሃሴ 24 ድረስ ሊቆይ እንደሚችል ፔሪሎ ተናግሯል። የሱዳን መገንጠል ጉዳይ አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል አጀንዳ ሊሆን እንደማይችል ጠቁመው፤ ግጭቱ ግን ሀገሪቱን ወደ ውድቀት ሊያመራት እንደሚችል ጠቁመዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik