ባይደን በርካታ ጦርነቶችን ለመዋጋት በማሰብ የአሜሪካን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የማስፋፋት አቅድ እንዳላቸው አንድ ዘገባ አመልክቷል

ባይደን በርካታ ጦርነቶችን ለመዋጋት በማሰብ የአሜሪካን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የማስፋፋት አቅድ እንዳላቸው አንድ ዘገባ አመልክቷልእ.ኤ.አ. ከ 2026 ጀምሮ የባይደን አስተዳደር ከብዙ አስርት አመታት በኋላ የአሜሪካ ስትራቴጂካዊ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን በከፍተኛ ደረጃ ለማስፋፋት ማቀዱን ኢኮኖሚስት በዘገባው ገልጿል። ከሩሲያ ጋር ያለው የስትራቴጂክ የጦር መሳሪያ ቅነሳ ስምምነት ጊዜው ካበቃ በኋላ እና አሜሪካ በአንድ ጊዜ ከሩሲያ፣ ከቻይና፣ ከኢራን እና ከሰሜን ኮሪያ የተጋረጠበትን የኒውክሌር ስጋቶችን ሳቢያ የአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የማስፋፋት እቅድ ውስጥ መግባታቸውን ዘገባው አመልክቷል።ቀደም ሲል የተደረጉት የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ቁጥጥር ስምምነቶች የጦር መሳሪያ ክምችቱን ቁጥሩን ቀንሶታል፤ እ.አ.አ በ1986 ከ70,000 የነበረው የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ክምችት ዛሬ ላይ ወደ 12,000 ዝቅ እንዲል ማስቻሉን አመልክቷል። ነገር ግን የቻይና የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እ.አ.አ በ2020 ከነበረበት ከጥቂት መቶዎች አድጎ፤ እ.አ.አ በ2030 ወደ 1,000 የሚደርስ ሲሆን፤ በ2035 ደግሞ ወደ 1,500 ይደርሳል ተብሎ እንደሚገመት ዘገባው አክሎ አትቷል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik