በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ሁለት ቋሚ መቀመጫዎችን እንደምትፈልግ የሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ተናገሩአፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ፍትሃዊ ውክልና እና ትርጉም ያለው ተሳትፎን የሚያረጋግጥ የተሃድሶ ራዕይ እና ሞዴል በግልፅ እና አሳማኝ በሆኑ ምክንያቶች ሳቢያ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ሁለት ቋሚ መቀመጫዎች እና ተጨማሪ ሁለት ተለዋጭ መቀመጫዎች ያስፈልጓታል ሲሉ የሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ባዮ በኒውዮርክ በተካሄደው የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።"የለውጡ ጊዜ አሁን ነው። አፍሪካ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣን(የቪቶ ሥልጣን) እንዲቀር ወይም ይህ ሥልጣን ለሁሉም አዲስ ቋሚ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት እንዲሰጥ ጥሪዋን ታስተላልፋለች" ያሉ ሲሆን አክለውም "የአፍሪካ ድምጽ ሊሠማ ይገባል። የፍትህና የፍትሃዊነት ጥያቄዎች መመለስ ይባቸዋል። "ብለዋል።ባዮ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ዙሪያ የአፍሪካ ህብረት ያቋቋመውን የአስር ሀገራት መሪዎች ኮሚቴ አስተባባሪ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia