ሩሲያ እና ኤርትራ ኢኮኖሚያዊና ሰብዓዊ ትብብራቸውን የበለጠ ለማሳደግ ተስማሙ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጸው በሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚክሄል ቦግዳኖቭ እና በኤርትራ ጉዳይ ፈጻሚ ናይዝጊ ሓጎስ መካከል በሞስኮ ውይይት ተደርጓል። ባለስልጣናቱ የንግድ፣ የኢኮኖሚ እና የሰብዓዊ ትብብራቸውን ስለማስፋት ተወያይተዋል። "ሞስኮ እና አስመራ የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋግጥ የንግድ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሰብዓዊ ትብብራቸውን አጠናክሮ የመቀጠል ፍላጎት እንዳላቸው በውይይቱ ወቅት ገልጸዋል። [ሁለቱ ወገኖች] በጋራ የዓለም አቀፍ እና የአፍሪካ አጀንዳዎች ላይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በሌሎች የባለብዙ ወገን መድረኮች የፖለቲካ ውይይት እና የተቀራረበ ቅንጅታቸውን ማጠናከር ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል" ሲል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አስነብቧል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia