አፍሪካውያን ጋዜጠኞች በሩሲያ ፋብሪካ ተገኝተው አዳዲስ የግብርና ማሽነሪዎችን ጎበኙ

አፍሪካውያን ጋዜጠኞች በሩሲያ ፋብሪካ ተገኝተው አዳዲስ የግብርና ማሽነሪዎችን ጎበኙከዛምቢያ፣ ኮንጎ፣ ታንዛኒያ እና ኢትዮጵያ የተውጣጡ የጋዜጠኞች ቡድን ሩሲያ በዓለም ላይ ያላትን ሰብአዊ ተፅእኖ የማጠናከር ተልእኮ በተሰጠው የሩሲያ የፌደራል ኤጀንሲ ሮስሶትሩድኒቼስቶቭ አማካኝነት ወደ ሩሲያ ተጉዘዋል። ሴንት ፒተርስበርግ ከተማን መቀመጫው ያደረገውንና ከሩሲያ ዋና የማሽነሪ ማምረቻዎች አንዱ የሆነውን ኪሮቭ ፋብሪካን ጎብኝተዋል። ኩባንያው የኪሮቬት ብራንድ ምርቶቹን ለኢትዮጵያ፣ ሊቢያ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ደቡብ አፍሪካ አስረክቧል። ወደ ግብፅ እና ናይጄሪያ ምርቶቹን ለማቅረብ በድርድር ላይ እንደሚገኝ የገለጹት የፒተርስበርግ ትራክተር ፋብሪካ የሽያጭ ዳይሬክተር ጆኦርጂ ፔርቲናቫ በአህጉሪቱ አዳዲስ አጋሮችን እየፈለገ እንደሆነ ተናግረዋል። ጋዜጠኞቹ ታዉራስ-ፌኒክስ እና ታዉራስ-ፕላስት ፋብሪካዎችንም ጎብኝተዋል። ኩባንያዎቹ ሴንት ፒተርስበርግ ውስጥ ከሚገኙ ግዙፍ የፕላስቲክ ምርት እና ማሸጊያ አምራቾች መካከል ናቸው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik