የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከሩሲያ ጋር በመከላከያ እና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር እንደምትሰራ የሀገሪቱ ባለስልጣን ተናገሩ የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ሀገሪቱ ላይ ጥሎ የነበረውን የጦር መሳሪያ እገዳ ማንሳቱን ተከትሎ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የኮሙዩኒኬሽን እና የመገናኛ ብዙሃን ሚንስትር ማክሲም ባላው ለስፑትኒክ በሰጡት ቃል "አሁን ከሩሲያ እና ሌሎች ሀገራት ጋር የመከላከያ እና የፀጥታ ሀይላችንን ለማጠናከር እድሉን አግኝተናል" ብለዋል። የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ጦሯን በድጋሚ በመሳሪያ የማስታጠቂያ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እና "አንዳንድ የትጥቅ ትግል ቦታዎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለማጥፋት የሚያስችል በቂ አቅም" ለማቅረብ ትሰራለች ሲሉ ሚኒስትሩ አክለዋል። እ.አ.አ. 2013 በመንግሥት እና በተለያዩ ታጣቂ አማፂ ቡድኖች መካከል የተጀመረውን የእርስ በርስ ጦርነት ተከትሎ በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ላይ ተጥሎ የነበረውን የጦር መሳሪያ እገዳ የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ሐምሌ 30 ቀን በሙሉ ድምፅ አንስተዋል። ከሩሲያ በተጨማሪ ቻይና፣ ጋቦን፣ ጋና እና ኬንያ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲነሳ የጠየቁ ሀገራት ናቸው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia